የት/ት መርሐግብሩ በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ልጆች እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሰውን የሚያፍሩ፣ በጥምቀት የተወለዱባትን ቅድስት ቤ/ክ ሥርዓት እና ሕግ በፍቅር የሚጠነቅቁ እና የሚያገለግሉ፣ ያሳደጋቸውን ቤተሰብ እና ማኅበረሰብ በጎ ዕሴቶች የሚጠብቁ በአጠቃላይ መንፈሳዊ ተግባራትን በዘላቂነት እንዲተገብሩ ለማስቻል የሚሰራ ሲሆን የት/ት መርሐግብሩ በተሰጠባቸው ያለፉት 4 ዙሮች በእግዚአብሔር እና በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ረዳትነት ከላይ የተጠቀሱት ሀሳቦች በልጆች ሕይወት ላይ እንዲንጸባረቁ እና ፍሬ እንዲያፈሩ እየተሰራ ይገኛል።
በቆይታቸው ልጆች መሠረታዊ የቤ/ክ ት/ቶችን፣ የአብነት ት/ትን የሚማሩ ሲሆን የሥዕል የሐረግ ጥበብ እና ሌሎች የተግባረ እድ ስልጠናዎችንም ይወስዳሉ። ከእነዚህም በተጨማሪ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የጎለመሱ በሕይወት ክህሎት የጠነከሩ ይሆን ዘንድ ስልታዊ የማስተማሪያ ዘዴዎችን እና የተለያዩ መርሐግብራት በመቅረጽ የተማሯቸውን ትምህርቶች ተግባራዊ በሆነ መንገድ እንዲረዷቸው እና ወደ ሕይወታቸው አምጥተው እንዲጠቀሙባቸው ትኩረት ተደርጎ ይሰራል።
ልጆች ፍቅረ ቤ/ክን እና መዓዛ ቤ/ክ በልቡናቸው ውስጥ የበለጠ ያድር ዘንድ በዕለተ ሰንበት ጉዞዎችን በማዘጋጀት አቅራቢያ ያሉ ገዳማትን አድባራትን እንዲሳለሙ የሚደረግ ሲሆን በት/ት መርሐግብሩ ማጠቃለያም ዐቢይ ጉዞ በማዘጋጀት ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቤ/ክ ገዳማትን እና ቅዱሳን መካናትን እንዲጎበኙ ይደረጋል።
ቦታ: አዲስ አበባ ፒያሳ | ቆይታ: 2 ወር
7
ተማሪዎች
0
ተመላላሽ
10+
አገልጋዮች
ቦታ: አዲስ አበባ ፒያሳ | ቆይታ: 2 ወር
17
ተማሪዎች
5
ተመላላሽ
12+
አገልጋዮች
ቦታ: አዲስ አበባ | ቆይታ: 2 ወር
80
ተማሪዎች
0
ተመላላሽ
50+
አገልጋዮች
ቦታ: አዲስ አበባ | ቆይታ: 2 ወር
154
ተማሪዎች
120
ተመላላሽ
100+
አገልጋዮች
ቦታ: አዲስ አበባ | ቆይታ: 6 ሳምንት
250
ተማሪዎች
300
ተመላላሽ
200+
አገልጋዮች

01.
መንፈሳዊ ት/ቶችን መማር ብቻ ሳይሆን የተማሯቸውን ትምህርቶች እንዴት በሕይወት መኖር እንዳለባቸው መንገድ የሚያሳዩ መንፈሳዊ የሕይወት ልምምዶችንም ያደርጋሉ።
02.
ራስን ችሎ ነገሮችን የመከወን፣ ማንኛውንም አይነት ቦታ እና ሁኔታን ተላምዶ እና ተቋቁሞ የመኖር ክህሎቶችን ያሳድጋሉ።
03.
እነርሱን ለማገልገል ዋጋ የሚከፍሉ አገልጋዮችን እና እነርሱን ለመጎብኘት ዋጋ ከፍለው የሚመጡ የክብር እንግዶችን፣ ሊቃውንት መምህራንን እና ትልልቅ አባቶችን እና እናቶችን በማየት አሁን ባላቸው አውም ቤ/ክንን ለማገልገል ራሳቸውን ዝግጁ ያደርጋሉ ነገ አድገው ለቅድስት ቤ/ክ ደርሰውላት በብዙ አቅም ለማገልገል ይዘጋጃሉ።
04.
መሠረታዊ የቤ/ክ ትምህርቶች ላይ፣ የአብነት ት/ት ላይ እና የተግባረ እድ ትምህርቶች ላይ ስልታዊ የሆኑ የማስተማሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም መሠረታዊ እውቀቶች እንዲኖሯቸው ይሠራል።