ስለ ስልጠናው አዘጋጅ ተቋም

ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ

ሐመረ ብርሃን ማን ነው?

ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ተቋም "ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር" "ወደ ቀድሞው ነገር እንመለስ" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክንን ጥንታዊ እውቀት እና ጥበብ፣ የቅድስት ቤ/ክንን ትውፊት እና አስተምህሮ የጠበቁ ኦርቶዶክሳዊ የተግባረ እድ ውጤቶችን ለመስራት እና ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በ2011ዓ.ም በመሀል አዲስ አበባ ፒያሳ ላይ ሥራውን ጀመረ።

በዚህም ስራው ላለፉት 6 ዓመታት በ7 ዘርፎች፣ በ5 ቅርጫፎች፣ ከ80+ በሚሆኑ መደበኛ ሠራተኞች እና ከ400+ በሆኑ በጎ ፈቃደኛ አገልጋዮች ዓላማውን ለማስፈጸም እየሠራ ሲሆን ከእነዚህ ዘርፎችም አንዱ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሕጻናት ት/ት መርሐግብርን፣ ለወጣቶች የሚሰጡ የተግባረ እድ ስልጠናዎችን እና ሌሎች ሰፋፊ አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኘው የት/ት እና ስልጠና ክፍል ከሰባቱ ዘርፎች አንዱ ነው።

ስለ ሐመረ ብርሃን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ድኅረ ገጻችንን ይጎብኙ።

Hamere Berhan Manuscript Work

ስለ ስልጠናው አዘጋጅ ተቋም

የሐመረ ብርሃን ት/ት እና ስልጠና ክፍል

ሐመረ ብርሃን የሚሠራቸውን፣ ጊዜያዊ ሳይሆኑ ታሪካዊ የሆኑና ለትውልድ የሚተላለፉ ድንቅ ሥራዎችን አሁን ያለው ትውልድ እንዲያውቃቸውና የሙያ ባለቤትም በመሆን የዚህ ጥበብ ማዕድ ተካፋይ እንዲሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን እና ስልጠናዎችን እየሠጠ ይገኛል። የሚሰጡት ት/ት እና ስልጠናዎችም የቀደምት አባቶቻችንን ጥንታዊ ጥበባት እና እውቀቶችን አሁን ያለው ትውልድ እንዲያያቸው እና እንዲያውቃቸው፣ ለሥራዎችቻቸውም ያለው ክብር እንዲያድግ፣ በዚህ ዘመን ትውልድ እና በቀደምት አባቶች መካከል ያለው የጥበብ ሰንሰለት ሳይበረዝ እንዲቀጥል እና ትውልዱ የአባቶቹን ሥራ ተመልክቶ ከመደነቅ ባለፈ የሚከውን እንዲሆን የሚያደርጉ ናቸው። ትምህርት እና ስልጠና ክፍሉ ወጣቶች ላይ እንዲሁም የዚህ ሥራ ዋና ተረካቢ እና አስቀጥይ የሆኑ ሕጻናት ላይ እየሠራ የሚገኝ ሲሆን

እስካሁን በስልጠና ጊዜ ውስጥ

  • 🌟
    ከ250+ የሚደርሱ ወጣቶችን እና
  • 🎨
    300+ ሕጻናትን በክረምት ት/ት መርሐግብሩ ማዕቀፍ ውስጥ አሰልጥኗል።

የሐመረ ብርሃን ማኅበራዊ ድኅረ ገጾች

Kids participating in summer camp activities

ስለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዘመነ ክረምት መርሐግብር

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዘመነ ክረምት መርሐግብር ከ7 እስከ 14 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ህፃናት የተዘጋጀ የክረምት ካምፕ (Summer Camp) ነው። መርሐግብሩ ልጆች እንደፍላጎታቸው በአዳሪነት ወይም በተመላላሽነት እንዲሳተፉ እድል ይሰጣል።

ለምን የክረምት እና የአዳር መርሐግብር ተመረጠ?

  • ልጆች ክርስቲያናዊ የኅብረትና የአንድነት ሕይወትን በኑሮ እየተለማመዱ ለመንፈሳዊ እድገታቸው በጋራ እንዲተጉ ለማድረግ።
  • ተማሪዎች ከመስከረም እስከ ሰኔ ባለው ጊዜ በመደበኛ ትምህርታቸው ስለሚጠመዱ፣ በክረምት ወቅት የተሻለ ጊዜና ትኩረት መስጠት ይችላሉ።
  • የአዳር መርሐግብሩ ልጆቹን በቅርበት ለማግኘትና በሚፈለገው መንፈሳዊና ሥነ ምግባራዊ መስመር ለመቅረጽ የተሻለ ዕድል ስለሚሰጥ።

ልጅዎን ያስመዝግቡ!

ልጆቻችንን ለመቀበል ዝግጁ ሁነን እየጠበቅን ነው።

ቦታ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ